ሁለተኛው ብሄራዊ የዪኒቨርስቲ እና ኢንዱስትሪ ትስስር የውይይት መድረክ በካይዘን የልህቀት ማዕከል ተካሄደ

የኢትየጵያ ቴክስታይል እና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከኢንዳስትሪ ሚኒስቴር፣ የአምራች ኢንዳስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት እና የአማራ ኢንዳስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮ ጋር በመተባበር ሁለተኛውን ብሄራዊ የዪኒቨርስቲ እና ኢንዱስትሪ ትስስር የውይይት መድረክ በ፲፮//፳፻፲፮ / በካይዘን የልህቀት ማዕከል አዘጋጅቷል፡፡


በዝግጅቱም ላይ ከትምህርት ተቋማት፣ ከመንግስታዊ እና ከግል ድርጅቶች የመጡ ባለሙያዎች ተሳትፈውበታል፡፡ በዚህ ውጤታማ በሆነ የምክክር መድረክ ላይ በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቴክስታይል እና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ከአምራች ኢንዳስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት እና አፍሪካ የቆዳ እና የቆዳውጤት ኢንስቲትዩት ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረመዋል፡፡ ስምምነቱም አጋር አካላቱ ከዚህ በፊት ሲያከናውኗቸው ከነበሩ ተግባራት በተሻለ የተለያዩ ስራዎችን ለመስራት እንደሚያግዝ ተጠቅሷል፡፡