ኢንስቲትዩቱ ከኢትዮጵያ ሌዘር ኢንዱስትሪ ደቨሎፕመንት ኢንስቲትዩት ጋር በትብብር ለመስራት ውይይት አካሄደ

ኢንስቲትዩቱ ከኢትዮጵያ ሌዘር ኢንዱስትሪ ደቨሎፕመንት ኢንስቲትዩት /LIDI / ጋር በትብብር ለመስራት የሚያስችል ውይይት አካሄደ፡፡ 

(ኢትዮጵያ ቴክስታይልና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት, መጋቢት 06/2014 ዓ/ም)

የኢትዮጵያ ቴክስታይልና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት እና የኢትዮጵያ የሌዘር ደቨሎፕመንት ኢንስቲትዩት ዓመራሮች በቆዳና ቆዳ ውጤቶች ዘርፍ ላይ ተቋማቱ በጋራ አብረው በሚሰሩባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይት አደረጉ፡፡

ሁለቱ ተቋማት ከአሁን በፊት በቆዳና ቆዳ ውጤቶች በተመለከተ በትብብር እየሰሩ ይገኛሉ፡፡ በመሆኑም ተቋማቱ ከአሁን በፊት በተጀመሩ የጋራ ስራዎችን የበለጠ በማጠናከር እንዲሰሩ እና በቀጣይም በቆዳና ቆዳ ውጤቶች ዙሪያ ያለውን ሀገራዊ ችግር ለመፍታት የተለያዩ የጥናትና ምርምር ስራዎችን በጋራ መስራት፤ የትምህርት ዕድል እና የሙያ ማሻሻያ አጫጭር ስልጠናዎች በጋራ መስራት እና ሀገራዊ የምክክር ፎረሞችን በጋራ ማዘጋጀት በሚሉ ጉዳዮች ላይ ሰፋ ያለ ውይይት ተደርጓል፡፡

በቀጣይ ሁለቱ ተቋማት በጋራ በሚሰሩባቸው ጉዳዮች ላይ የሁለትዮሽ የስምምነት ሰነድ በማዘጋጀትና በመፈራረም አብረው የሚሰሩ ይሆናል፡፡

Share