News page

ተማሪዎችን ማዕከል ያደረጉ የማነቃቂያ ንግግሮች ቀረቡ

[ሚያዝያ 2/2014 ዓ.ም፣ ባህር ዳር - ኢስኮ/ባቴኢ]የባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የሙያ ማጎልበቻ ማዕከል ባሰናዳው ፕሮግራም ላይ በቅድሚያ ንግግር ያቀረቡት የTalent Firm መስራችና ዋና ሥ/አስኪያጅ ወ/ሪት ሩት ዮሃንስ ሲሆኑ በቀጣሪዎች ፍላጎት እና ተቀጣሪዎች እርከን መካከል ያለውን ልዩነት ከጥናታቸው ውጤት ጋር በማጣቀስ አቅርበዋል፡፡ እንደ ወ/ሪት ሩት ገለጻ ተማሪዎች በስራ ገበያው ተወዳዳሪ መሆን እንዲችሉ የቡድን ስራ፣ ችግር ፈቺነት፣ የፈጠራ ችሎታ፣ የማወቅ ፍላጎትና የተግባቦት ብቃታቸውን ከፍ ለማድረግ ዘወትር መስራት እንደሚጠበቅባቸው አስረድተዋል፡፡

Pages