ማስታወቂያ
ማስታወቂያ
በ 2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምደባ ወቅት አዎንታዊ ድጋፍ እንዲደረግላችሁ የምትፈልጉ ተመሳሳይ ጾታ መንትዮች፣ የሚያጠቡ እናቶች እንዲሁም የተለያዩ የጤና ዕክል ያለባቸው ተማሪዎች የ 2017 ዓ.ም 12ኛ መልቀቂያ ፈተና ውጤት እስኪገለጽ ድረስ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት እያደረጋችሁ እንድትጠባበቁ እናሳስባለን።
የሚያስፈልጉ ሰነዶች
1. ለተመሳሳይ ጾታ መንትያ አመልካቾች
1.1. የሁለቱም አመልካቾች የልደት ካርድ
1.2. ከሚማሩበት ትምህርት ቤት የድጋፍ ደብዳቤ
2. የሚያጠቡ እናት አመልካቾች
2.1. ስድስት (6) ወር ያልሞላው የህጻኑ/ኗ የክትባት ካርድ
2.2. ከተማሩበት ትምህርት ቤት የድጋፍ ደብዳቤ
3. የተለያዩ የጤና ዕክል ያለባቸው አመልካቾች
3.1. ከመንግስት ሆስፒታሎች የቦርድ ወሳኔ የተሰጠበት የህክምና የምስክር ወረቀት