የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በ2018 የትምህርት ዘመን በሁለተኛዉ ወሰነ ትምህርት በግል ከፍለው ወይም በመስሪያ ቤታቸው ስፖንሰር አድራጊነት ከፍለው መማር ለሚፈልጉ
1ኛ. በመደበኛው መርሃ ግብር የ2ኛ ዲግሪ እና የ3ኛ ዲግሪ አመልካቾችን፤
2ኛ. በማታው መርሃ ግብር የ2ኛ ዲግሪ እና የ3ኛ ዲግሪ አመልካቾችን፤
ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከታህሳስ 24/2018 ዓ.ም እስከ የካቲት 10/2018 ዓ/ም ድረስ ማመልከት የሚችሉ መሆኑን እያሳወቅን አመልካቾች የሚያመለክቱባቸውን የትምህርት መስኮች ዝርዝር እና የመግቢያ መስፈርቶችን ከዩኒቨርሲቲው ሬጅስትራር ድረ ገጽ https://bdu.edu.et/registrar/ መመልከት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡ የመመዝገቢያ ጊዜ ከየካቲት 26-27/2018 ዓ/ም ሲሆን ትምህርት የሚጀምረዉ የካቲት 30/2018 ዓ/ም ነው፡፡ ለተማሪዎች የማንበቢያና መመራመሪያ ቢሮ እና የዶርም አገልግሎት ዩኒቨርስቲዉ የሚሰጥ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
Remarks: We will admit 20 students to the MEd in Educational Sciences—Teaching of Mathematics and the MED in Educational Sciences—Teaching of Science Subjects, both supported by the BDU-NORHED scholarship program.
ለምዝገባ የሚያስፈልጉ ሰነዶች/ማስረጃዎች፣
የትምህርት ማስረጃ ዋናውንና ፎቶ ኮፒ፤
ኦፊሻል ትራንስክሪፕት
በመስሪያ ቤት ስፖንሰርነት ለሚያመለክቱ አመልካቾች ከሚሰሩበት መስሪያ ቤት የስፖንሰርሽፕ ደብዳቤ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
የ National Graduate Admission Test (NGAT) የማለፊያ ውጤት ያለው/ያላት፣
ለማመልከቻ የተከፈለበት ደረሰኝ (Application fee 300 ብር)፣
photo