የመጽሐፍ ምረቃ ስነ-ስርዓት

31 Jul, 2025

የመጽሐፍ ምረቃ ስነ-ስርዓት
ፍኖተ ጥበብ የታዋቂው ድምጻዊ አርቲስት ይሁኔ በላይ አዲስ መጽሐፍ ቅዳሜ ሐምሌ 26/2017ዓ/ም ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ በባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ዊዝደም አዳራሽ ይመረቃል።
በመሆኑም ድምፃዊ አርቲስት ይሁኔ በላይ በባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ በአካል በመገኘት መጽሐፋቸውን ያስመርቃሉ። የዩኒቨርስቲያችን አመራሮች ፣ ምሁራን ፣ ሰራተኞች፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት በደማቅ ሁኔታ ይመረቃል።
የዩኒቨርስቲው ማህበረሰብ በሙሉ ተጋብዛችኋል።