
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በአማራ ክልል በጦርነት የተጎዱ አካባቢዎች መልሶ ማቋቋምና ግንባታ ፈንድ ጽ/ቤት ጋር አብሮ መስራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ፡፡
31 Jul, 2025
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በአማራ ክልል በጦርነት የተጎዱ አካባቢዎች መልሶ ማቋቋምና ግንባታ ፈንድ ጽ/ቤት ጋር አብሮ መስራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ፡፡
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ከአማራ ክልል በጦርነት የተጎዱ አካባቢዎች መልሶ ማቋቋምና ግንባታ ፈንድ ጽ/ቤት (Amhara Regional State War Affected Areas Rehabilitation and Reconstruction Fund Office) ጋር አብሮ መስራት የሚያስችል ስምምነት በዊዝደም የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተፈራረሙ፡፡
የስምምነት ፊርማውን የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ዶ/ር መንገሻ አየነ እና የአማራ ክልል በጦርነት የተጎዱ አካባቢዎች መልሶ ማቋቋምና ግንባታ ፈንድ ጽ/ቤት (Amhara Regional State War Affected Areas Rehabilitation and Reconstruction Fund Office) ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት ዶ/ር አባተ ጌታሁን በጋራ ለመስራት ተፈራርመዋል፡፡
የስምምነቱ ዓላማ ከፍተኛ ውድመት የደረሰባቸውን እና የጉዳቱ መንስኤዎችን ለማወቅ ያለመ ነው፤ ማህበረሰቡን ለከፍተኛ ጉዳት ተጋላጭ ያደረጉ ፖለቲካዊ፣ ታሪካዊ እና መዋቅራዊ ሁኔታዎችን መለየት በማስፈለጉ እንዲሁም የጋራ ጥናት በማድረግ የጉዳቱን መጠን እና ተፅእኖ በሳይንሳዊ መንገድ ለመገምገም ተጨባጭ መረጃዎችን ለመጠቀም በማስፈለጉ እንደሆነ ከስምምነት ሰነዱ መረዳት ተችሏል፡፡
ከዚህም ባሻገር በስምምነት ሰነዱ ዘላቂ ልማትን፣ ሰላምን፣ ደህንነትንና መረጋጋትን ለማረጋገጥ፤ እንዲሁም መሠረተ ልማቶችን፣ ተቋማትን እና ባለ ብዙ ሽፋን አገልግሎቶችን እንደገና መገንባት እና ሌሎች አስፈላጊ ጉዳዮችን በጋር መስራት በፊርማ ስነ ስርአቱ ተነስተዋል።
በፊርማ ስምምነቱ ንግግር ያደረጉት ከአማራ ክልል በጦርነት የተጎዱ አካባቢዎች መልሶ ማቋቋምና ግንባታ ፈንድ ጽ/ቤት ዋና ስራ አስኪያጅ ዶ/ር አባተ ጌታሁን ከባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጋር በርካታ ስራዎችን ሰርተናል እየሰራንም እንገኛለን የዛሬው ስምምነት በጋራ አቅዶ ለመስራት የሚያስችል ነው ብለዋል፡፡


