
የድምጻዊ ይሁኔ በላይ የጥበብ ፍኖት የተሰኘ መጽሐፍ ምረቃ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተካሂዷል።
03 Aug, 2025
ባሕር ዳር: ሐምሌ 26/2017 ዓ.ም (አሚኮ) በምረቃ ሥነ-ስርዓቱ ድምጻዊ ይሁኔ በላይ እና የቀድሞ የግሽ ዓባይ የኪነት ቡድን አባላት ተገኝተዋል::
ዩኒቨርሲቲው ድምጻዊው ለባሕል ሙዚቃ ዕድገት ላበረከተው አስተዋፅኦ እውቅና ያበረከተለት ሲሆን የአገው ፈረሰኞች ማኅበርም የማኅበሩ አምባሳደር በማድረግ እውቅና ሰጥቶታል።
የኢትዮጵያ ደራሲያን ማኅበር ፕሬዝዳንት ደራሲ አበረ አዳሙ የመጽሐፉን ዳሰሳ አቅርበዋል። በዳሰሳቸውም መጽሐፉን ከግለታሪክ የአጻጻፍ ይትባህ አንጻር ቃኝተውታል።



