ለመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ
መስከረም 5 ቀን 2018 ዓ.ም
ማስታወቂያ
ለመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በ2018 ዓ/ም የትምህርት ዘመን ትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው የመግቢያ መስፈርት መሰረት በመደበኛ መርሃ ግብር በግላቸው ከፍለው በመደበኛው መርሃግብር የመጀመሪያ ዲግሪ መማር የሚፈልጉ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም መስፈርቱን የሚያሟሉና በግላችው ከፍለው መማር የሚፈልጉ አመልካቾች መስከረም 6 ቀን 2018 ዓ/ም እስከ መስከረም 12 ቀን 2018 ዓ/ም ድረስ የሚፈልጉትን የትምህርት ፕሮግራም (Department) በመምረጥ ማመልከት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
የመግቢያ መስፈርት
- በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ የማጠቃለያ ፈተና ወስደው የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ መቁረጫ ነጥብ ያሟሉ፤
- በ2017 ዓ.ም የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ወስደው የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ነጥብ ያላቸው፤