በ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በትምህርት ሚኒስቴር ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ አዲስ የአቅም ማሻሻያ (Remedial Program) ተማሪዎች ምዝገባ ከህዳር 11 እስከ ህዳር 12/2018 ዓ.ም የሚካሄድ መሆኑን እናሳውቃለን።
የምዝገባ ቦታ፦
ለማህብራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ግሽ አባይ ግቢ
ለተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ዘንዘልማ ግቢ
ማሳሰቢያ፡-
ተማሪዎች ለምዝገባ ስትመጡ
ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ
የ8ኛ እና 12ኛ ክፍል ካርድ ዋናውንና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ፣
ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውንና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ፣
አራት 3x4 የሆነ ጉርድ ፎቶ ግራፍ ይዛችሁ መምጣት ይኖርባችኋል።
የሬጅስትራርና አልሙናይ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ
27/02/2018 ዓ.ም
photo