Submitted by TANA on

 

ለአቅም ማሻሻያ (Remedial) ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ :-

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በግል ከፍለው በማታው መርሀ-ግብር በአቅም ማሻሻያ (Remedial) መማር ለሚፈልጉ ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም በትምህርት ሚኒስትር የወጣውን መስፈርት የምታሟሉ አመልካቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ጀምሮ እስከ ህዳር 5 ቀን 2018 ዓ/ም ድረስ ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ለምዝገባ የሚያስፈልጉ ሰነዶች/ማስረጃዎች፣

● የትምህርት ማስረጃ ዋናውንና ፎቶ ኮፒ፤

● ለማመልከቻ የተከፈለበት ደረሰኝ (Application fee 300 ብር)

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሂሳብ ቁጥር፦1000224663378

የክፍያ መጠን፦ ለተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች 4,480

ለማህበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች 3,720

የማመልከቻ ቦታ፦

● በተከታታይና ርቀት ማስተባበሪያ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 13 በአካል በመቅረብ መሆኑን እንገልፃለን፡፡

የሬጅስትራርና አልሙናይ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ

ቀን፡- 24/02/2018 ዓ.ም