Submitted by TANA on

መስከረም 5 ቀን 2018 ዓ.ም
ማስታወቂያ
ለመጀመሪያ ዲግሪ መደበኛ ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በ2018 ዓ/ም የትምህርት ዘመን ትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው የመግቢያ መስፈርት መሰረት በመደበኛ መርሃ ግብር በግላቸው ከፍለው በመደበኛው መርሃግብር የመጀመሪያ ዲግሪ መማር የሚፈልጉ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም መስፈርቱን የሚያሟሉና በግላችው ከፍለው መማር የሚፈልጉ አመልካቾች መስከረም 6 ቀን 2018 ዓ/ም እስከ  መስከረም 12 ቀን  2018 ዓ/ም ድረስ የሚፈልጉትን የትምህርት ፕሮግራም (Department) በመምረጥ ማመልከት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
የመግቢያ መስፈርት
-  በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ የማጠቃለያ ፈተና ወስደው የከፍተኛ ትምህርት  መግቢያ መቁረጫ ነጥብ ያሟሉ፤
-  በ2017 ዓ.ም የአቅም ማሻሻያ (Remedial) ፕሮግራም ወስደው የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ነጥብ ያላቸው፤
ለማመልከት የሚያስፈልጉ፣
የ12ኛ ክፍል ካርድ ወይም የአቅም ማሻሻያ ውጤት ዋናውንና ኮፒ
የማመልከቻ ክፍያ፤ 300.00 (ሶስት መቶ) ብር
የማመልከቻ ቦታ፤ 
የጀማሪ መርሃግብር ሬጅስትራር ጽ/ቤት በአካል ወይም ማስረጃውን ስካን በማድረግ  በኢሜል bduregistrar@bdu.edu.et  ከማመልከቻ ጋር በመላክ ማመልከት ይቻላል፡፡
ማሳሰቢያ፡- 
ተማሪዎች የሚማሩት የትምህርት መስክ በመረጡት ይሆናል፡፡
በርካታ አመልካቾች ያሉባቸው ፕሮግራሞች በውድድር የሚለዩ ይሆናል።
በአቅም ማሻሻያ ውጤት ለሚገቡ ኦፊሺያል ትራንስክሪፕት(Official Transcript) ከምዝገባ በፊት ማስላክ ይኖርባቸዋል፡፡ 
ህክምና ትምህርት ለመማር የሚያመለክቱ አመልካቾች የትምህርት ክፍሎችን ዝቅተኛ መግቢያ መስፍርት ማለፍ ይጠበቅባቸዋል
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራርና አልሙናይ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት