Submitted by TANA on

መስከረም 5 ቀን 2018 ዓ.ም
ማስታወቂያ
ለመጀመሪያ ዲግሪ ነጻ የትምህርት ዕድል ፈላጊዎች በሙሉ
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ለ2018 ዓ/ም የትምህርት ዘመን በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ የማጠቃለያ ፈተና ወስደው ለወንዶች 480 እና ከዚያ በላይ  እንዲሁም ለሴቶችና አካል ጉዳተኞች 450 እና ከዚያበላይ ያስመዘገቡ ተማሪዎችን በመንግስት ስፖንሰር አድራጊነት የትምህርት ዕድል (ስኮላርሽፕ) በመስጠት በመደበኛ መርሃ ግብር ማስተማር ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም መስፈርቱን የሚያሟሉና ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ መማር የሚፈልጉ አመልካቾች ከመስከረም 6 ቀን 2018 ዓ/ም እስከ መስከረም 12 ቀን  2018 ዓ/ም ድረስ ማመልከት የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ለማመልከት የሚያስፈልጉ፣
የ12ኛ ክፍል ካርድ ውጤት ኮፒ
የማመልከቻ ቦታ፤ 
የጀማሪ መርሃግብር ሬጅስትራር ጽ/ቤት በአካል ወይም ማስረጃውን ስካን በማድረግ  በኢሜል  bduregistrar@bdu.edu.et  ከማመልከቻ ጋር በመላክ ማመልከት ይቻላል፡፡
ማሳሰቢያ፡- 
የትምህርት ፕሮግራም  ምደባ  ከሌሎች  የመደበኛ  ተማሪዎች  ጋር  በውድድር  የሚመደቡ  ይሆናል፡፡
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራርና አልሙናይ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት