ሰኔ 23 ቀን 2017 ዓ.ም
የጥሪ ማስታወቂያ
ለነባር ክረምት የመጀመሪያና ሁለተኛ ዲግሪ ተማሪዎች በሙሉ
የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የ2017 ዓ/ም የክረምት ትምህርት የሚጀምረውና ምዝገባ የሚካሄደው
ከሐምሌ 14 - 15 ቀን 2017 ዓ/ም መሆኑን እየገለጽን ተማሪዎች ለምዝገባ ስትመጡ
በትምህርት ሚኒስቴር ስፖንሰር የሆናችሁ መገጣጠሚያ ደብዳቤ፤
በተለያዩ መስሪያ ቤቶች ስፖንሰር ተደርጋችሁ የምትማሩ ደግሞ መስሪያ ቤቱ ለ2017
ዓ/ም የትምህርት ክፍያ የተከፈለበት ደረሰኝ ይዛችሁ መምጣት እንዳለባችሁ ከወዲሁ
እናሳስባለን፡፡
ማሳሰቢያ፤
በትምህርት ሚኒስቴር ስፖንሰር ከተደረጉ ተማሪዎች በስተቀር ዩኒቨርሲቲው የዶርምና የምግብ
አገልግሎት የማይሰጥ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
ከተጠቀሰው የምዝገባ ጊዜ በፊትም ሆነ ዘግይቶ የሚመጣን ተማሪ የማንቀበል መሆኑን
እናሳውቃለን፡፡
የባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ
ሬጅስትራርና አልሙናይ ማኔጅመንት ዳይሬክቶሬት
photo
