Professor Mamo Muchie gave a motivational speech to EiTEX Community.

በሀገር ወዳድነታቸው የሚታወቁት ዕውቁ ኢትዮጵያዊው ፕሮፌሰር ማሞ ሙጨ በኢትዮጵያ ቴክስታይልና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት “ኢትዮጵያዊነትና የፈጠራ ስራዎች ማዘመን ” በሚል ርዕሰ በኢንስቲትዩቱ ፋሽን አዳራሽ ህዝበ ገለፃ አደረጉ፡፡

ፕሮፌሰሩ ኢትዮጵያዊ የሆኑ ነባር እሴቶችና ማህበረሰባዊ ዕውቀቶችን በማዘመን እና ለፈጠራ በመጠቀም ረገድ የሚስተዋሉ ችግሮችን በማንሳት መፍትሔ ያሉትን ሃሳብ ለታዳሚዎች አካፍለዋል፡፡

በገለፃቸው ወቅት ሁሉን አቀፍ የሆነ ኢትዮጵያዊ የፈጠራ ስርዓት መዘርጋት በሚቻልባቸው መንገዶች ላይ ፕሮፌሰሩ ማብራሪያ አቅርበዋል፡፡

ፕሮፌሰር ማሞ እኛ ዜጎቿ ሀገራችን በውል ዕምቅ አቅሟን በማወቅ ረገድ ክፍተት መኖሩን በቁጭት ተናግረዋል፡፡

 ቀደምት አባቶቻችን የነበራቸውን ትምህርታዊ ጥበብ እና ባህላዊ እሴቶች አስመልክቶ ሰፊማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ወጣቱ የአባቶቻችን ፈለግ በመከተል የተሻለች ኢትዮጵያን በመገንባት ሂደት ጉልህ አስተዋፅኦ ኢንዲያበረክት ፕፌሰሩ አደራ ብለዋል፡፡

የኢንስቲትዩቱ ሣይንቲፊክ ዳይሬክተሩ ዶ/ር ታምራት ተስፋዬ ፕሮፌሰር ማሞ ሙጨ እና ሌሎች መሰል ኢትዮጵያዊ ሙሁራን ወደ ሀገራቸው በመምጣት ወጣቱን ትውልድ በማነፅና የነገ ሀገር ተረካቢ በማፍራት ስራ ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በዕለቱ ከ700 የሚበልጡ ተማሪዎች ፤ መምህራንና ከተለያዩ የዩኒቨርሲቲው የስራ ክፍሎች የመጡ ታዳሚዎች የህዝበ ገለፃው ተሳታፊ ሁነዋል፡፡

የኢንፎርሜሽንና ስትራቴጂክ ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር (ኢስኮድ)

ለተጨማሪ መረጃዎች ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/eitex.et

Date: 
Sat, 03/26/2022
Image: 
Place: 
Bahir Dar University
Share