የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ 60ኛ ዓመትን ምክንያት በማድረግ የቴክኖሎጂ ቢዝነስ ሐሳብ ውድድር ማስጀመርያ ፕሮግራም ተካሄደ

[ሚያዝያ 6/2014 ዓ.ም፣ ባህር ዳር - ኢስኮ/ባቴኢ]
*************************************************
በBiTec አዘጋጅነት በተካሄደው ፕሮግራም ላይ እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት የመክፈቻ ፕሮግራም ያደረጉት የባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ስይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር ሠይፉ አድማሱ የፕሮግራሙ ዋና ዓላማ ለባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ 60ኛ ዓመት በዓል አከባበር ድምቀት የሚሆን ውድድር በማካሄድ ታላላቅ የሆኑ የቴክኖሎጅ የፈጠራ ውጤቶችን እውን ለማድረግ ታስቦ የሚካሄድ እንደሆነ ገልጸዋል። ይህም በተደራጀ መልኩ ከሄደ እንደ ዕቅድ እስከ እ.ኤ.አ. 2025 ራሳቸውን የቻሉ እና ማሕበረሰቡን የሚያግዙ ድርጅቶችን ማቁቋም ያስችላል ብለዋል። የኢንስቲትዩቱ ምክትል ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር ዶ/ር መኳንንት አገኘሁ በበኩላቸው ቴክኖሎጂ ነክ የሆኑ የሥራ ፈጠራ ሐሳቦችን ከሥራ ክህሎት ጋር በማጣመር ኢንስቲትዩቱ ረጅም ያለመ እንደመሆኑ መጠን BiTec ወጣት ኢንትርፕሬነሮችን ለመፍጠር እና ለማገዝ የተቋቋመ ነው። ከዚህም ጋር ተያይዞ የተለያዩ Hackathon እና Makaton ጨምሮ የተለያዩ ፕሮግራሞችን ማካሄዱ ጠቁመዋል። በዚህም 3 የሚሆኑ ቡድኖች በሐገር ዓቀፍ ደረጃ በሚዘጋጀው Bruh National Competition ውድድር በመሳተፍ 2ኛ 5ኛ እና 8ኛ መዉጣታቸውን ገልጽዋል። ከተውዳደሩት መካከል የAgelgil Eco Packaging እና Ray cosmetics መሥራች የሆኑት ወ/ት አፎሚያ እና ወ/ት ራውላ ሥራቸውን ለዓዲሶቹ ሠልጣኞች አቅርበዋል። በዚህም የነበረባቸውን ፈተና እና የገጠማቸውን ችግር በመግለጽ አዳዲስ ሠልጣኞች ረጅም አቀደው ከፊት በሚገጠማቸው እንከን እንዳይደናቀፉም ምክራቸውን ለግሰዋል። የBiT Makerspace አስተባባሪ ወ/ት ቤዛወርቅ በበኩላቸው BiTec የአፍሪካ Makerspace አባል መሆኑን በመግለጽ ከግለሰብ ጀምሮ ከተለያዩ ተቋማት እርዳታ እንዳልተለየው ገልጸዋል። ይህም በሐገር ደረጃ ብቻ ሳይሆን በአፍሪካ ደረጃ ለውድድር የበቃ ሥራ መቀረቡን በመጠቆም በመጪው ግዜ በሐገር ደረጃ አሸናፊ የሆኑት Agelgil Eco Packaging እና Ray cosmetics በአፍሪካ ደረጃ የገቡበትን ውድድር አሸናፊ እንደሚሆኑ እምነታቸውን ገልጸዋል። ዶ/ር በረከት በበኩላቸው የHuman Centered Design (HCD) ምንነት ለታዳሚው ያብራሩ ሲሆን ከጊዜያት በፊት እንደነበረው ባህላዊው የአሰራር ዜዴ ሳይሆን ተጠቃሚዎች በምርጫ የታጀቡ እንደመሆናቸው መጠን ማርካት የሚችል እና የተሻለ ሥራ አስፈላጊ ይሆናል በማለት የወ/ት ራውላን ሐሳብ ባጠናከረ መልኩ ሰዎች የሚሰሯቸውን ሥራዎች ከተጠቃሚው አንጻር ማድረግ አስፈላጊ ምሆኑን ገልፀዋል። ሥልጠናው ለ 4 ቀን የሚቆይ ሲሆን በሚያዝያ 7 ቀን 2014ዓም የመስክ መልከታ እንደሚኖር ተገልጿል። በውድድር ውስጥ 53 ተማሪዎች በ12 የቢዝነስ ቡድኖች የተዋቀሩ ሲሆኑ በተዘጋጀው መስፈርት መሠረት እንደሚመዘኑ ታውቋል።
የኢንፎርሜሽንና ስትራቴጂክ ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት (ኢስኮ)
ፌስቡክ፡- www.facebook.com/bitpoly
ቴሌግራም፡- https://t.me/bitpoly
ዌብሳይት፡- https://bit.bdu.edu.et