
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ አሳታሚ ድርጅት አቋቋመ
17 Sep, 2025
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ አሳታሚ ድርጅት አቋቋመ
የመጀመሪያ ሥራው የአፄ ዘርአ ያዕቆብ ዜና መዋዕል ሆነ
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ መጻሕፍትን በማዘጋጀትና በማሳተም ለማሰራጨት የሚያስችለውን “ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ” የተሰኘ አሳታሚ ድርጅት ማቋቋሙን አስታወቀ። ፕሬሱ የመጀመሪያ ሥራው አድርጎ “የዐፄ ዘርአ ያዕቆብ ዜና መዋዕል (1426 - 1460 ዓ.ም) ግእዝ-አማርኛ ትርጉም እና ሐተታ” የተሰኘ መጽሐፍ አሳትሞ ለገበያ አብቅቷል።
ይህ መጽሐፍ ከግእዝ ወደ አማርኛ የተተረጎመ ሲሆን፣ የመካከለኛውን ዘመን ታላቁን ንጉሥ አፄ ዘርአ ያዕቆብ የዘመን ታሪክና የእለት ከዕለት እንቅስቃሴ በዝርዝር ያቀርባል። 157 ገጾችን የያዘው ይህ ታሪካዊ ሰነድ፣ በመካከለኛው ዘመን የኢትዮጵያ ታሪክ ላይ ለሚደረጉ ጥናቶች ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለው ተገልጿል።
መጽሐፉ በአሁኑ ጊዜ በባሕር ዳር ከተማ በሚገኙ የመጻሕፍት መደብሮች በ350 ብር እየተሸጠ ሲሆን፣ በቅርቡ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ በደማቅ ሥነ ሥርዓት የሚመረቅ ይሆናል።
መጽሐፉን
በአዲስ አበባ
• ሀሁ የመጽሐፍ መደብር
• ማዮን የመጽሐፍ መደብር
• ኦሜጋ የመጽሐፍ መደብር
በባሕር ዳር
• አዳነ የመጽሐፍ መደብር
• ዮፍታሔ የመጽሐፍ መደብር
•ዮቶር የመጽሐፍ መደብር
ያገኙታል።
ከዓባይ ጓዳ ጥበብ ሲቀዳ!