የተማሪዎች የስነ ምግባር አምባሳደር ለመለየት ውድድር ተካሄደ
12 Nov, 2025
የተማሪዎች የስነ ምግባር አምባሳደር ለመለየት ውድድር ተካሄደ
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲን በመወከል የስነ ምግባር አምባሳደር ለመሆን ከሁሉም ግቢዎች የተመለመሉ ተማሪዎች በዋናው ግቢ አዳራሽ ውድድር አካሄዱ፡፡
በውድድሩ ተገኝተው የፕሮግራም ትውውቅ ያደረጉት የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ስራ አስፈፃሚ አቶ አለማየሁ ተፈራ ውድድሩን የሚያወዳድሩት ከማህበራዊ ሳይንስ ፋካልቲ የመጡ መምህራን ሲሆን ጥያቄዎችም በስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና የስራ ክፍል እንደተዘጋጀ ተናግረዋል፡፡
ኃላፊው አክለውም ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ከሚገኙ ሁሉም ግቢዎች የስነ ምግባር ክበብ አባል የሆኑ በውድድሩ እንዲሳተፉ በማድረግ እስከ ስድስትኛ የወጡትን፤ በማዕከል ጥያቄዎች ተዘጋጅተው በዩኒቨርሲቲ ደረጃ ከአንድ እስከ አስር የወጡትን ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲን በመወከል የስነ ምግባር አምባሳደር እንዲሆኑ ለፌድራል ስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ለመላክ ውድድሩ መካሄዱን ገልፀዋል፡፡
የውድድሩ ተማሪዎች ጥሩ ስነ ምግባር ኑሯቸው ሌሎቹን እንዲያስተምሩ የሚጠቅም ሲሆን ሙስናን ለመከላከል ወጣቶች ላይ ግንዛቤ መፍጠር አይነተኛ መንገድ በመሆኑ ነው፡፡ ይህ ውድድር በየአመቱ የሚካሄድ ሲሆን ባለፈው አመት በፌደራል ደረጃ በተዘጋጀው የዩኒቨርሲቲዎች የስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ውድድር ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሰርተፍኬት አግኝቷል የስነ ምግባር እና ፀረ ሙስና ስራ አስፈፃሚ አቶ አለማየሁ ተፈራ እንደገለፁት፡፡

