“በርዕይ ጥበብ ቁጥር ሁለት የተሻለ እድገትና አፈጻጸም ለማስመዝገብ የዩኒቨርሲቲው አመራርና ማህበረሰብ በህብር መስራት ወሳኝ ድርሻ አለው” ዶ/ር መንገሻ አየነ - የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት

27 Aug, 2025

ነሐሴ 21/2017 ዓ.ም ፤(ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ)፡ ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ለመቀበልና አዲሱን ዓመት ስራዎች ለመከወን የሚያስችለውን ቅድመ ዝግጅት ስራ ምክክር አድርጓል፡፡ 
የ2018 ዓ.ም ነባርና ዓዲስ ተማሪዎችን ለመቀበል የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች፣ ዲኖች፣ ም/ዲኖች እንዲሁም የትምህርት ክፍል ተጠሪዎች በተገኙበት በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ጥበብ አዳራሽ ውይይት የተካሄደ ሲሆን በአካዳሚክ ዘርፍ፣ በአስተዳደርና ልማት ዘርፍ እንዲሁም በምርምርና ማህበረሰብ ተሳትፎ ዘርፍ የተከናወኑ ቅድመ ዝግጅት ተግባራት ለመድረኩ ቀርበዋል፡፡ 
መድረኩን የመሩት የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲው ፕሬዚደንት ዶ/ር መንገሻ አየነ ሲሆኑ በቅድመ ዝግጅት ምዕራፍ የሚሰሩ ተግባራት በስራ ትግበራ ምዕራፍ ትልቅ እገዛ የሚሰጥ መሆኑን በማውሳት በመማር ማስተማር፣ በምርምርና ማህበረሰብ አሳታፊነት፣ በአስተዳደርና ልማት የተቋሙ ወሳኝ ዘርፎች ትኩረት ሰጥቶ በመስራት በጥበብ ርዕይ ቁጥር ሁለት አፈጻጸም የላቀ ውጤት ማስመዝገብ ተገቢ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ በዚህም የዩኒቨርሲቲው አመራር በየደረጃው፣ ሰራተኞች መምህራን የሚጠበቅባቸውን ሃላፊነት መወጣት እንደሚጠበቅባቸው አስረድተው ከአደራ ጭምር አሳስበዋል፡፡ የመማር ማስተማር ዘርፉን አጠናክሮ ለማስቀጠል በየደረጃው የሚገኙ የአስተዳደር ክፍሎች ድጋፍ በመስጠት የጋራ ትብብር በማድረግለዩኒቨርሲቲው እቅድ መሳለጥ መትጋት ያስፈልጋል ብለዋል ዶ/ር መንገሻ፡፡ 
በመድረኩ ተሳታፊዎች የጥገና፣ የውሃ እና የመብራት አቅርቦት፣ የቤተሙከራ፣ መማሪያ ክፍሎች፣ በአብያተ መጻህፍት ጉዳዮች ተነስተው ቤዘርፉ ቀሪ የዝግጅት ስራዎች በፍጥነት እንዲከናወኑ ፕሬዚደንቱ ስራ መመሪያ ሰጥተዋል፡፡ 
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የራስ ገዥ ዩኒቨርሲቲ የሽግግር ስራዎችን በመስራት ላይ ሲሆን አሁን የሚሰሩ ተግባራት ሁሉ ልናሳካ ለምንፈልገው የራስ ገዝ አቅምን እውን ለማድረግ ያለሙ መሆን እንደሚገባቸው በውይይቱ ተነስቷል፡፡ 
ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ-BDU
ከዓባይ ጓዳ ጥበብ ሲቀዳ 
Wisdom at the source of the Blue Nile!
Thank you for inviting, liking, sharing, and visiting the BDU page! 
በሌሎች አማራጮቻችንም ያግኙን
Telegram ፡- t.me/BDU_ISC_Official
Facebook: - https://www.facebook.com/bduethiopia
YouTube ፡- www.youtube.com/c/BduEduEt
LinkedIn ፡- www.linkedin.com/school/bahir-dar-university
Twitter: - https://twitter.com/bdueduet
website :- www.bdu.edu.et
Bahir Dar Institute of Technology, Bahir Dar University, Ethiopia

hibir1hibir2hibir3