በአፍላቶክሲን ብክለት ላይ የሚደረገውን ትግል የሚያግዝ ተስፋ ሰጪ አዲስ መሣሪያ በባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ተመራማሪዎች ይፋ ተደረገ

25 Sep, 2025

በአፍላቶክሲን ብክለት ላይ የሚደረገውን ትግል የሚያግዝ ተስፋ ሰጪ አዲስ መሣሪያ በባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ተመራማሪዎች ይፋ ተደረገ 

(መስከረም 15/2018ዓ.ም ISC/BiT) በአፍላቶክሲን ብክለት ላይ የሚደረገውን ትግል የሚያግዝ ተስፋ ሰጪ አዲስ መሣሪያ በባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ተመራማሪዎች ፣ ዊዝደም ኢንተርፕራይዝ ከ Stichting Wageningen Research (SWR) Ethiopia's RAISE-FS project ባገኘው የኢኖቬሸን ፈንድ ድጋፍ ታግዞ ይፋ ተደርጎ በዛሬው ዕለት ለአውደ ርዕይ ቀርቧል። ይህ አዲስ ፈጠራ፣ ቀላል፣ ወጪ ቆጣቢ የሆነው የእርጥበት መለኪያ ኪት፣ የደረቁ ምግቦችንና መኖ ምርቶችን ከብክለት ለመከላከል ታስቦ የተዘጋጀ ነው።

በቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት በኬሚካልና ምግብ ምህንድስና ፋኩልቲ ተመራማሪዎች በምርምር ተፈትሾ ተግባራዊነቱ የተረጋገጠ፣ አጠቃቀሙ ቀላል እንዲሁም የተጠቃሚዉን የመግዛት አቅምን ያገናዘበ በእህል፣ ጥራጥሬ፣ ቅመማ ቅመም፣ የደረቁ የአትክልትና ፍራፍሬ ውጤቶች፣ እንዲሁም የመኖ ምርቶችን በመበከል ተመጋቢዎችን ለካንሰር ተጋላጭ በማድረግና ወጪ ንግድን በማስተጓጎል የሚታወቀው አፍላቶክሲንን መከላከል የሚያስችል ቀላል ቴክኖሎጂ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ይህ ቴክኖሎጂ ለአፍላቶክሲን መበከል መንሰኤ የሆነውን የእርጥበት መጠን በማሳወቅ ከላይ የተጠቀሱት የምግብና መኖ ዓይነቶች ለክምችት ከመዘጋጀታቸው ወይንም በማከማቻ ከረጢት ከመታሽጋቸው በፊት በበቂ ሁኔታ መድረቃቸውን ለማረጋገጥና በክምችት ወቅትም ተቀያያሪ የሆነውን የርጥበት መጠን ለመከታተል የሚያስችል ዘዴ መሆኑ ተገልጿል።

ይህንን የርጥበት መለኪያ በአቅርቦት ሰንሰለት ላይ ያሉ ተዋናዮች፣ በተለይም አርሶ አደሮች፣ የአርሶአደር መሰረታዊ ማህበራትና ስብሳቢ ነጋዴዎች እንዲጠቀሙት የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተቋም የሆነው ዊዝደም ኢንተርፕራይዝ ለገበያ ማቅረብ መቻሉ ተጠቅሷል።

toxin1toxin2toxin3